የተከበራችሁ የአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አንቀፅ 366፣367፣370 እና 372 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለው የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 18 መሠረት የአጋር ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 22ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢንተር ሌግዥሪ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡